ስፓርት

ማንቼስተር ሲቲ እና ኒውካስል ዩናይትድ ነጥብ ተጋሩ

By Mikias Ayele

September 28, 2024

አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በ6ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማንቼስተር ሲቲ እና ኒውካስል አቻ ተለያይተዋል፡፡

ቀን 8 ሰዓት ከ30 ላይ በተደረገው ጨዋታ ማንቼስተር ሲቲ በዮስኮ ጋቫርዲዮል ጎል ቀዳሚ መሆን ቢችልም ከእረፍት መልስ አንቶኒ ጎርደን ፍፁም ቅጣት ምቱን ወደ ጎል ቀይሮ ባለሜዳዎቹን አቻ አድርጓል፡፡

ውጤቱን ተከትሎ ማንቼስተር ሲቲ ፕሪሚየርሊጉን በ14 ነጥብ በጊዜያዊነት መምራት ሲችል ኒውካስል ነጥቡን ወደ 11 ከፍ በማድረግ 5ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡