Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ትልቅ ተስፋ በተሰነቀበት የኮደርስ ስልጠና ላይ ሁሉም በመሳተፍ እድሉን ሊጠቀም ይገባል ተባለ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ለዜጎችም ይሁን ለሀገር ትልቅ ተስፋ በተሰነቀበት የኮደርስ ስልጠና ላይ ሁሉም በመሳተፍ እድሉን ሊጠቀም እንደሚገባ ተገለጸ።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ይፋ በተደረገው የዲጂታል ክህሎት ማሳደጊያ የ5 ሚሊየን የኮደርስ ስልጠና ኢኒሼቲቭ መርሐ ግብር “ትውልድ ይማር፣ ትውልድ ይሰልጥን፣ ከዓለም ጋር ይፎካከር” በሚል እሳቤ በሁሉም የሀገሪቷ አካባቢዎች እየተካሄደ ይገኛል።

የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አለሚቱ ኡሞድ÷ በክልሉ መርሃ ግብሩ ይፋ ከተደረገ ጀምሮ የስልጠና እድሉን ሁሉም እንዲጠቀመው የግንዛቤ መፍጠር ስራ መከናወኑን ገልጸዋል።

የኮደርስ ስልጠና በተለይም ለወጣቶች የቀጣይ ህይወት መሰረት የሚያኖር በመሆኑ በክልሉ የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርጉ እየተሰራ ነው ብለዋል።

የኮደርስ ስልጠና ከግለሰብ ጀምሮ እንደ ሀገር ጠቀሜታው ከፍ ያለ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በዚህ ዓለም አቀፍ ደረጃውን በጠበቀ የኮደርስ የስልጠና ሂደት የክልሉ ወጣቶች፣ ተማሪዎችና ሌሎችም የህብረተሰብ ክፍሎች እድሉን እንዲጠቀሙ ርእሰ መስተዳድሯ ጥሪ አቅርበዋል።

 

Exit mobile version