ስፓርት

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ዛሬ ይካሄዳሉ

By Shambel Mihret

September 28, 2024

አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ስድስተኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ ይካሄዳሉ።

ቀን 8 ሰዓት ከ30 ላይ ኒውካስል ዩናይትድ የሊጉን መሪ ማንቼስተር ሲቲን የሚያስተናግድበት ጨዋታ ይጠበቃል።

እንዲሁም ቀን 11 ሰዓት ላይ አርሰናል ሌስተር ሲቲን፣ ብሬንትፎርድ ዌስትሃም ዩናይትድን፣ ቼልሲ ብራይተንን፣ ኤቨርተን ክሪስታል ፓላስን እንዲሁም ኖቲንግሃም ፎረስት ፉልሃምን የሚያስተናግዱባቸው ጨዋታዎች ይካሄዳሉ።

ምሽት 1 ሰዓት ከ30 ላይ ደግሞ ዎልቭስ ሊቨርፑልን የሚያስተናግድበት ጨዋታ ይደረጋል።

ሊጉን ማንቼስተር ሲቲ በ13 ነጥብ እየመራ ሲሆን ሊቨርፑል፣ አስቶን ቪላ እና አርሰናል ከሁለት እስከ አራት ያለውን ደረጃ ይዘው ይከተላሉ።