አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ‘አርቲሜተር’ የተባለ በመርፌ የሚሰጥ የወባ መድሐኒት ጥቅም ላይ እንዳይውል ታገደ።
የኢትዮጵያ ምግብና መድሐኒት ባለስልጣን እንዳስታወቀው፤ በገበያ ቅኝት የተደረሰበት በፈረንጆቹ 2023 ህዳር ወር የተመረተው የባች ቁጥር 231104SPF መድሐኒት በባለስልጣኑ ያልተመዘገበ ነው።
የመድሐኒቱን ናሙና በመውሰድ በላቦራቶሪ በተደረገ ፍተሻ ‘አርቲሜተር’ የተባለው ንጥረ ነገር በውስጡ ያልተገኘበት መሆኑን የባለስልጣኑ መረጃ ጠቁሟል።
በመሆኑም መድሐኒቱን የጤና ባለሙያዎች እንዳይጠቀሙ አስገንዝቧል።
በተጨማሪም በየደረጃው ያሉ የክልል ተቆጣጣሪዎች በየአካባቢያቸው ጥብቅ ክትትል በማድረግ እርምጃ እንዲወስዱ አሳስቧል።