አዲስ አበባ፣ መስከረም 17፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር በካናዳ የሁለት ቀናት የሥራ ጉብኝት አድርገዋል፡፡
በጉብኝታቸው ከካናዳ ምክር ቤት አፈ -ጉባዔ ጌርግ ፈርጉሰን እና ከሌሎች የመንግስት ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ጋር በሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ዙሪያ መክረዋል፡፡
በተጨማሪም በኢትዮጵያና ካናዳ የፌዴራል ሥርዓትና አሰራር ዙሪያ የተወያዩ ሲሆን÷ በዚህም በሀገራቱ ምክር ቤቶች መካከል ያለውን ትብብር ማጠናከር እንደሚገባ ተጠቁሟል።
ካናዳ በኢኮኖሚ ልማትና ሰብዓዊ መስኮች ለኢትዮጵያ እያደረገች ለሚገኘው ድጋፍ አፈ-ጉባዔ አገኘሁ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
በቀጣይ በቴክኖሎጂ፣ በንግድ እና ኢንቨስትመንት ዘርፎች የሀገራቱን ግንኙነት ለማስፋት እንደሚሰራም ተናግረዋል።
አዳዲስ የትብብር መስኮችን ለመለየት 8ኛ የኢትዮ- ካናዳ የፓለቲካ ምክክር መድረክ በቅርብ ጊዜ ማካሄድ አስፈላጊ እንደሆነ መጠቀሱንም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡