Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ቅዱስ ጊዮርጊስ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 17፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ቅዱስ ጊዮርጊስ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲን 2 ለ1 አሸንፏል፡፡

10 ሰዓት ላይ በድሬዳዋ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ የቅዱስ ጊዮርጊስን የማሸነፊያ ግቦች ፍፁም ጥላሁንና አማኑኤል ኤርቦ አስቆጥረዋል፡፡

ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲን ከሽንፈት ያልታደገችዋን ብቸኛ ግብ ደግሞ ኪሩቤል ወንድሙ ከመረብ አሳርፏል፡፡

የሊጉ መርሐ ግብር ሲቀጥል ምሽት 1 ሰዓት ላይ ባሕር ዳር ከተማና አዳማ ከተማ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡

Exit mobile version