ስፓርት

የሲቲው አማካይ ሮድሪጎ ሄርናንዴዝ ከውድድር ዓመቱ ተሳትፎ ውጪ ሆነ

By Melaku Gedif

September 27, 2024

አዲስ አበባ፣ መስከረም 17፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ስፔናዊው የማንቼስተር ሲቲ አማካይ ሮድሪጎ ሄርናንዴዝ ባጋጠመው የጉልበት ጉዳት ከ2024/25 የውድድር ዓመት ተሳትፎ ውጪ መሆኑን ክለቡ አስታውቋል፡

ተጫዋቹ ጉዳቱን ያስተናገደው ማንቼስተር ሲቲ በሜዳው ከአርሰናል ጋር ባደረገው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ላይ ነበር፡፡

የ28 ዓመቱ የዩሮ 2024 አሸናፊ ሮድሪ ማንቼስተር ሲቲ በቅርብ ዓመታት ላስመዘገበው ስኬት ቁልፉ ተጫዋች መሆኑ ይነገራል፡፡

ሮድሪጎ ሄርናንዴዝ የጉልበት ቀዶ ጥገና በስፔን ማድሪድ ማድረጉን ቢቢሲ በዘገባው አመላክቷል፡፡

ጉዳቱን ተከትሎም ሮድሪ ከውድድር ዓመቱ ተሳትፎ ውጪ መሆኑን የክለቡ አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ አስታውቀዋል፡፡