የሀገር ውስጥ ዜና

የ ‘ጋሪ ዎሮ’ በዓል በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው

By ዮሐንስ ደርበው

September 27, 2024

አዲስ አበባ፣ መስከረም 17፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የሺናሻ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ ‘ጋሪ ዎሮ’ በዓል በአሶሳ ከተማ በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው፡፡

በበዓሉ አከባበር ላይ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አሻድሊ ሀሰንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ የብሔረሰቡ ተወላጆች እንዲሁም የተለያዩ ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

እንደ ክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ በዓሉ በተለያዩ ባህላዊ ዝግጅቶች እየተከበረ ይገኛል።