ስፓርት

በፕሪሚየር ሊጉ ስሑል ሽረ እና ሐዋሳ ከተማ አቻ ተለያዩ

By ዮሐንስ ደርበው

September 27, 2024

አዲስ አበባ፣ መስከረም 17፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሁለተኛ ሳምንት ጨዋታ ስሑል ሽረ እና ሐዋሳ ከተማ አንድ አቻ ተለያይተዋል።

ስሑል ሽረ ፋሲል አስማማው በ48ኛው ደቂቃ ባስቆጠራት ጎል ሲመራ ቢቆይም÷ የስሑል ሽረው መሐመድ ሱሌይማን በ93ኛው ደቂቃ በራሱ ላይ ባስቆጠራት ግብ ሐዋሳ ከተማ ነጥብ እንዲጋራ አስችሎታል፡፡

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሁለተኛ ሳምንት መርሐ-ግብሮች ሲቀጥሉ÷ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ 10 ሠዓት እንዲሁም ባሕር ዳር ከተማ ከአዳማ ከተማ 1 ሠዓት ላይ ይጫወታሉ።