አዲስ አበባ፣ መስከረም 17፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የመስቀል በዓል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በመላ ሀገሪቱ እየተከበረ ይገኛል፡፡
በዓሉ በተለያዩ ሐይማኖታዊ እና ባህላዊ ሥነ-ሥርዓቶች ነው በድምቀት እየተከበረ የሚገኘው።
በትናንትናው ዕለት የመስቀል ደመራ በመላ ሀገሪቱ በደማቅ ሥነ-ሥርዓት መከበሩ ይታወሳል፡፡
መስቀል ከቁሳዊ ይልቅ መንፈሳዊ ኃይል እንደሚበልጥ ማሳያ መሆኑን ትናንት በመስቀል ደመራ በዓል ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ገልጸዋል፡፡
በዓለም ላይ እርስ በርስ አለመተማመን እንዲፈጠር ያደረገው በመስቀሉ ላይ የሚተላለፈው መልዕክት ገቢራዊ ባለመደረጉ መሆኑንም አንስተዋል፡፡
በዛሬው ዕለትም ሕዝበ-ክርስቲያኑ እርስ በርስ በመደጋገፍ እና በመረዳዳት የመስቀል በዓልን ማክበር እንደሚገባው አስረድተዋል፡፡