የሀገር ውስጥ ዜና

አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከሕንድ አቻቸው ጋር ተወያዩ

By Shambel Mihret

September 26, 2024

አዲስ አበባ፣ መስከረም 16፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከሕንድ አቻቸው ሱብራማንያ ጄይሻንካር (ዶ/ር) ጋር ተወያይተዋል፡፡

በኒውዮርክ እየተካሄደ ከሚገኘው 79ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ጠቅላላ ጉባዔ ጎንለጎን ነው አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከሕንድ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሱብራማንያ ጄይሻንካር (ዶ/ር) ጋር የተወያዩት፡፡

ሁለቱ ሚኒስትሮች የጋራ ፍላጎት በሚሹ ሁለትዮሽ እና ባለብዙ ወገን ግንኙነት ዙሪያ መምከራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡