የሀገር ውስጥ ዜና

የመስቀል በዓል ማህበራዊ ግንኙነትን፣ አንድነትንና የጋራ እሴትን የሚያጎላ መሆን አለበት- ርእሰ መስተዳድር አወል አርባ

By Shambel Mihret

September 26, 2024

አዲስ አበባ፣ መስከረም 16፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የመስቀል በዓልን የእምነቱ ተከታዮች ሲያከብሩ ማህበራዊ ግንኙነትን አንድነትና ወንድማማችነትን በሚያጠናክር የጋራ እሴታችን በሚያጎላ መልኩ መሆን እንዳለበት የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገለጹ፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ ለመስቀል በዓል ባስተላለፉት መልእከት÷በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በየዓመቱ በድምቀት ከሚከበሩ በዓላት አንዱ የደመራና የመስቀል በዓል መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የእምነቱ ተከታዮች በዓሉን ሲያከብሩ ማህበራዊ ግንኙነት አንድነትና ወንድማማችነት በሚያጠናክር የጋራ እሴታችን የሚያጎላ መሆን አለበትም ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽ መረጃ ያመላክታል፡፡

የተቸገሩና ድጋፍ የሚሹ ወገኖቻችን በመንከባከብና በመርዳት አንዱ ለአንዱ ያለውን ወንድማማችነት አንድነት የሚያጠነክሩ መልካም እሴቶችን የሚያጎሉ የመተሳሰብና የመረዳዳት ተግባራትን የሚያጠናክር እንዲሆንም አስገንዝበዋል፡፡