የሀገር ውስጥ ዜና

የመስቀል በዓልን ስናከብር ሰላምና እድገትን ዘላቂ ለማድረግ ቃል በመግባት ነው – አቶ ጌታቸው ረዳ

By Shambel Mihret

September 26, 2024

አዲስ አበባ፣ መስከረም 16፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የመስቀል በዓልን ስናከብር ሰላም፣ ልማትና እድገት ዘላቂ ለማድረግ ቃል በመግባት ነው ሲሉ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታቸው ረዳ ገለጹ።

በትግራይ ክልል የመስቀል በዓል በተለያዩ አካባቢዎች በድምቀት ተከብሯል።

በመቐለ ጮምዓ ተራራ ዛሬ አመሻሽ ላይ በተከበረው የመስቀል በዓል ላይ የሐይማኖት መሪዎች፣ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ አባላትና የክርስትና እምነት ተከታዮች ተገኝተዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ ጌታቸው ረዳ በበዓሉ ላይ ተገኝተው ለህዝበ ክርስቲያኑ ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችህ መልዕክት፤ በዓሉን ስናከብር በፍቅር፣ በመተሳሰብና በአብሮነት መሆን አለበት ብለዋል፡፡

በተለይም በየደረጃው የምንገኝ የአመራር አካላት የተግባር ሰዎች በመሆን ለህዝብ ያለንን ተዓማኒነት ልናረጋግጥ ይገባል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በክልሉ የሚገኙ የፀጥታ አካላት የህዝብን ሰላም ለማስፈን የሚያደርጉትን የሚደነቅ እንቅስቃሴ ይበልጥ አጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባም አስገንዝበዋል።