አዲስ አበባ፣ መስከረም 16፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና ለኢትዮጵያ በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ቼን ሃይ ገለጹ፡፡
የስራና ክሎት ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ፥ በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ከሆኑት ቼን ሃይ ጋር ሁለቱ ወገኖች በጋራ መስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መመክራቸውን ገልጸዋል፡፡
በዚህም በቻይና እድገትና ልማት ውስጥ የቴክኒከና ሙያ ትልቅ አበርክቶ እንደነበረውና ኢትዮጵያም ለዘርፉ ትኩረት ሰጥታ እየሰራች እንደሆነ በውይይቱ ወቅት ማንሳታቸውን ጠቅሰዋል፡፡
ቻይና ለኢትዮጵያ በዘርፉ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ቼን ሃይ በውይይቱ ወቅት አረጋግጠዋልም ነው ያሉት፡፡
የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት በላቀ ደረጃ ለማሳደግም ቻይና ቁርጠኝነት እንዳላትም አምባሳደሩ መግለጻቸውን ወ/ሮ ሙፈሪያት ጠቁመው ÷አምባሳደሩ በትብብር ለመስራት ላሳዩት ቁርጠኝነት ምስጋና አቅርበዋል፡፡