Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለመስቀል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 16፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለመስቀል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በመልዕክታቸውም÷ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ፣ ደሙን አፍስሶ፣ ለሰዉ ልጆች ሁሉ ፍቅሩን ገልጿል ብለዋል፡፡

ይህ ሁሉ ዋጋ የተከፈለበት መስቀል ምሳሌነት በዚህች ምድር ስንኖር እርሰበርሳችን ያለ ምንም ልዩነት በፍቅር፣ በምህረት እና በመተሳሰብ እንድንኖር ነውም ሲሉ ገልጸዋል፡፡

መላው የከተማዋ ነዋሪዎች የከተማዋ ሌላኛው ድምቀት የሆነው የመስቀል ደመራ በዓል እንደ ምሳሌነቱ የሰው ልጆችን ሁሉ በመውድ፣ እርስበርስ በመተባበር፣ በመከባበርና በፍቅር የዓሉን እሴቶች በመጠበቅ ባማረና በደመቀ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ የበኩላችሁን እንድትወጡ ጥሪዬን አቀርባለሁ ብለዋል፡፡

በዓሉ ፍቅር፣ የደስታ እና አብሮነት የሚጎላበት የተዋበ በዓል ይሁንልን ሲሉም ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

Exit mobile version