አዲስ አበባ፣ መስከረም 16፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረሪ ክልላዊ መንግስት ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ለመስቀል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፏል፡፡
የክልሉ መንግስት በመልእክቱ÷ ህዝበ ክርስቲያኑ የመስቀል ደመራ በዓል እሴቱን ጠብቆ እንዲከበር በማድረግ የተቸገሩ ወገኖችን በማብላትና የተጠሙትን በማጠጣት እንዲሁም የተለመደ የመተዛዘንና የመረዳዳት ባህሉን እንዲተገብር ጥሪ አቅርቧል።
ህዝበ ክርስትያኑን ጨምሮ መላው የክልሉ ነዋሪ ሰላምን፣ አብሮነትን፣ መተባበርንና ወንድማማችነት እና እህትማማችነትን በማጎልበት እንዲያከብርም አሳስቧል፡፡
በክልሉ የተጀመሩ ሁሉን አቀፍ የልማት ተግባራት መጠናከር እንዳለባቸው መግለጹንም የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
የክልሉ መንግስት በዓሉ የሰላም፣ የአንድነት፣ የመተሳሰብ፣ የደስታና የፍቅር እንዲሆን ተመኘቷል።