Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የተለያዩ ሀገራት ኤምባሲዎችና ዓለም አቀፍ ተቋማት ለመስቀል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 16፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የተለያዩ ሀገራት ኤምባሲዎችና ዓለም አቀፍ ተቋማት ለመስቀል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልካም ምኞት መግለጫ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

የአውሮፓ ህብረት በማህበራዊ ትስስር ገጹ እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ ሲል መልዕክቱን አጋርቷል፡፡

በኢትዮጵያ የእስራኤል ኤምባሲ በበኩሉ፥ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለመስቀል (የደመራ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ ብሏል፡፡

በዓሉም የሰላምና የፍቅር እንዲሆን እስራኤል እንደምትመኝም አክሎ ገልጿል፡፡

በተመሳሳይ የፈረንሳይ ኤምባሲ፥ በዓሉን አስመልቶ ባስተላለፈው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት መልካም ምኞቱን ገልጿል።

Exit mobile version