Fana: At a Speed of Life!

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የጥንቃቄ መልዕክት

አዲስ አበባ፣ መስከረም 16፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰሞኑን የተለያዩ የዲጂታል ሚዲያዎችን በመጠቀም ሽልማቶችን ለመሸለም በሚመስል መልኩ የኢትዮ-ቴሌኮም ነጻ የዳታ ሽልማት ለሁሉም አሮጌ ሲም ካርድ ተጠቃሚዎች በሚል መልዕክቶች ወደ ተለያዩ ግለሰቦች እየተላኩ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር አረጋግጧል።

ይህ መልዕክትም የግለሰቦችን ሚስጥራዊ መረጃዎች የማጥመድ ጥቃት (Phishing Attack) መሆኑን ማረጋገጥ ችሏል።

በጥቃት አድራሾቹ ለተጠቃሚዎች አጓጊ የሚመስሉ ሆነዉ ከኋላቸዉ የሳይበር ጥቃት የያዙ ሲሆን የተጠቃሚዎችን ቀልብ ለመሳብ የኢትዮ ቴሌኮም ረጅም ጊዜ ተጠቃሚ በሚል በሲም ካርድ የቆይታ ጊዜ የሚል ዘዴዎችን እየተጠቀሙ ሲሆን ከእነዚህ መካከል፡-

• 6 ወር የቆየ ሲም- 10GB

• 1 አመት እና ከዚያ በላይ- 20GB

• 5 አመት እና ከዚያ በላይ- 50GB እንሽልማለን የሚሉ ናቸዉ።

ነገር ግን ያቀረቡት ማታለያ እንጂ ምንም አይነት ሽልማት እንደማይሰጡ ማህበረሰቡ እንዲያዉቅና ሊንክ ተጠቃሚዎችን ለማጥመድ ታስቦ የተዘጋጀ በመሆኑ በፍጹም ሊንኩን እንዳይከፍቱ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር አሳስቧል፡፡

እንደዚህ አይነት የማጭበርበር ሁኔታዎች በበዓል ወቅቶች በስፋት የሚከሰቱ በመሆኑ ማህበረሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግም መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.