Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የጎርጎራ ኢኮ ሪዞርት

አዲስ አበባ፣ መስከረም 16፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የገበታ ለሀገር ፕሮጀክት አካል የሆነው የጎርጎራ ኢኮ ሪዞርት በአማራ ክልል የሚገኝ ነው፡፡

የጎርጎራ ፕሮጀክት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) “ገበታ ለሀገር” በሚል ይፋ ካደረጓቸው ሶስት ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ መሆኑ ይታወቃል።

የገበታ ለሀገር ፕሮጀክቶች የመጀመሪያው ዙር ከአዲስ አበባ ውጪ ሶስት ቦታዎችን ከአማራ ክልል ጎርጎራ፣ ከኦሮሚያ ክልል ወንጪ እና ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ኮይሻን ለማልማት ወደ ተግባር በመግባት ፕሮጀክቶቹን እውን ማድረግ ተችሏል።

የጎርጎራና አካባቢው አስደናቂ ስፍራ ለዘመናት ልማት ርቆት ውበቱና ሃብቱ ሳይገለጥ የቆየ መሆኑና አሁን ላይ ለቱሪስቶች ምቹ መዝናኛ ሆኖ ተሰርቷል፡፡

የጎርጎራ ልማት ለጣና ተጨማሪ ሞገስ፣ ለጎንደር እና ባሕር ዳር ክብር፣ ለኢትዮጵያ ደግሞ የመቻል ማሳያዋ ነዉ፡፡ የጎርጎራ ኢኮ ሪዞርት እንደ ሀገር በፈተናዎች የመፅናት አቅም የተገለጠበት ውጤት ነው፡፡

ጎርጎራ ንፅፅር የማይሻ፣ ታሪካዊ ይዘቱን ጠብቆ የተገነባ፣ ውበትን በልዩ ጥበብ የታደለና ሳይደበዝዝ ለትውልድ የሚተላለፍ ድንቅ የዕጅ ስራ መሆኑም ይነገርለታል፡፡

በታሪካዊው ስፍራ ላይ በዘመናዊ መልኩ የተገነባው የጎርጎራ ኢኮ ሪዞርት ሁነኛ የቱሪስት መዳረሻም ነው፡፡

Exit mobile version