Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

5 ሚሊየን ቋሚ በጎ ፈቃደኞችን ለማፍራት መታቀዱ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 16፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በተያዘው በጀት ዓመት 5 ሚሊየን ቋሚ በጎ ፈቃደኞችን ለማፍራት ዕቅድ መያዙን የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) ገለጹ።

ሚኒስትሯ ከለውጡ ወዲህ የበጎ ፈቃድ ስራዎች ባህል እንዲሆኑ ሰፋፊ ስራዎች መሰራታቸውን ተናግረዋል፡፡

በተጠናቀቀው በጀት ዓመትም በክረምት በጎ ፈቃድ ስራዎች ከ 24 ሚሊየን በላይ ወጣቶች በ13 የተለያዩ ማህበራዊ ግልጋሎቶች ላይ በመሳተፋቸው ከ 50 ሚሊየን በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸዋል።

የበጎ ፈቃድ ስራዎች ቀጣይነት ባለው መንገድ እንዲከናወኑ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ፖሊሲ መቀረጹንም ሚኒስትሯ ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) መጠቆማቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በተያዘው በጀት ዓመት የተዘጋጁትን ፖሊሲና አዋጆች ወደ ስራ ለማስገባት በትኩረት እንደሚሰራና 5 ሚሊየን ቋሚ በጎ ፈቃደኞችን ለማፍራት እቅድ መያዙንም ተናግረዋል፡፡

Exit mobile version