Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የዘንድሮ ኢሬቻ መስከረም 25 እና 26 እንደሚከበር የአባገዳዎች ህብረት አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 16፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢሬቻ 2017 መስከረም 25 እና 26 እንደሚከበር የአባገዳዎች ህብረት አስታውቋል፡፡

አከባበሩን አስመልክቶ መግለጫ የሰጠው ህብረቱ÷ መስከረም 25 ኢሬቻ ሆረ ፊንፊኔ በማግስቱ መስከረም 26 ቀን 2017 ዓ.ም ደግሞ ኢሬቻ ሆረ አርሰዴ በድምቀት እንደሚከበር ገልጿል።

ህብረቱ በሆረ ፊንፊኔ እና በሆረ አርሰዴ ለሚከበረው በዓል ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁንም አስታውቋል፡፡

በዓሉን በሰላም፣ በአብሮነት፣ በወንድማማችነትና በአንድነት ማክበር እደሚገባም ህብረቱ አሳስቧል፡፡

ባህላዊ ትውፊቱን በጠበቀ የበዓሉን አልባሳት በመልበስ ማክበር እንደሚገባም የተገለጸ ሲሆን÷ በዓሉ ፈጣሪ የሚመሰገንበት ከቤተሰብ እስከ ሀገር እርቅ የሚወርድበት መሆኑም ተጠቁሟል፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብም በዓሉን በአንድነት እንዲያከብርም ጥሪ ቀርቧል።

በማርታ ጌታቸው እና ፈትያ አብደላ

Exit mobile version