የሀገር ውስጥ ዜና

ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ የተመድ ዋና ጸሐፊ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛን አመሰገኑ

By ዮሐንስ ደርበው

September 25, 2024

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ሃና ቴቴህ በቀጣናው ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋና አቀረቡ፡፡

መልዕክተኛዋ በቀጣናው የነበራቸውን የሥራ ጊዜ ማጠናቀቃቸውን ተከትሎ በፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ ስንብት ተደርጎላቸዋል፡፡

በዚሁ ወቅትም ለኢትዮጵያና ለአፍሪካ ቀንድ ላበረከቱት ከፍተኛ ድጋፍ ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ አመስግነዋል፡፡