የሀገር ውስጥ ዜና

ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ከሃይማኖት አባቶች ጋር ተወያዩ

By ዮሐንስ ደርበው

September 25, 2024

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ከመስቀል ደመራ በዓል አከባበር ጋር በተያያዘ ከሃይማኖት አባቶች ጋር ተወያይተዋል፡፡

በዓሉ ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲከበር በቂ የሰው ኃይል እና አነፍናፊ ውሾችን በመጠቀም የተጠናከረ ፍተሻ በማካሄድ አካባቢዎቹን የማጥራት ሥራ እየተሠራ መሆኑን ኮሚሽነር ጀነራሉ በውይይቱ ላይ ገልጸዋል፡፡

ፖሊስ የተለያዩ አደረጃጀቶችን በመፍጠር ኦሬንቴሽን በመስጠት ወደ ሥራ መግባቱን እና የፖሊስ ሠራዊቱ በፖሊሳዊ ሥነ-ምግባር በጨዋነት ፍተሻውን እንደሚያካሄድም አስረድተዋል፡፡

ፍተሻው ለጋራ ጥቅም መሆኑን በመገንዘብ ሕዝቡ ትብብር እንዲያደርግ መጠየቃቸውን ከፌደራል ፖሊስ ያገነኘው መረጃ አመላክቷል፡፡

የሃይማኖት አባቶች በበኩላቸው የፀጥታና ደኅንነት አካላት በዓሉ በሰላም እንዲከበር እያደረጉት ላለው ጥረት አመስግነው÷ በእነሱ በኩል የተከለከሉና የተፈቀዱ ነገሮችን ለምዕመናን ማስገንዘባቸውን ተናግረዋል፡፡