የሀገር ውስጥ ዜና

በደቡብና በምሥራቅ ሊባኖስ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጥሪ ቀረበ

By ዮሐንስ ደርበው

September 25, 2024

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ እና በምስራቅ የሊባኖስ አካባቢዎች የፀጥታ ችግር እየተጠናከረ መምጣቱን ተከትሎ በሀገሪቱ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጄኔራል ጽሕፈት ቤት ለዜጎቹ ጥሪ አቅርቧል፡፡

ጽሕፈት ቤቱ ባወጣው መረጃ በተለይም በደቡብ እና በምስራቅ የሊባኖስ አካባቢዎች የፀጥታ ችግር እየተጠናከረ መሆኑን ገልጾ÷ በእነዚህ አካባቢዎች ያሉ ዜጎችን ለይቶ ማወቅ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል ብሏል፡፡

በመሆኑም በአካባቢው የሚኖሩ ወገኖች ከታች በተቀመጠው መሠረት ስማቸውን ፓስፖርት ላይ አንደተፃፈው፣ የፓስፖርት ቁጥር እና ስልክ ቁጥራቸውን እንዲያስመዘግቡ ጥሪ አቅርቧል፡፡

በዚሁ መሠረት በደቡብ ሊባኖስ (ታየር፣ ሱር፣ ቢንት ጅቤል፣ ማርጃዩን፣ ነበትዬ፣ ሳይዳ እና አካባቢው) የሚገኙ ወገኖች በስልክ ቁጥር 03-7354 51 ወይም 03-87-10-89 እንዲሁም በምሥራቅ ሊባኖስ (አልቤክ፣ ቤካ ሸለቆ እና አካባቢው) የሚገኙ ደግሞ በስልክ ቁጥር 81 77-62-51 ወይም 81-63-07-98 በመደወል እንዲመዘገቡ አሳስቧል፡፡