የሀገር ውስጥ ዜና

በትራፊክ አደጋ የ7 ሰዎች ህይወት አለፈ

By Feven Bishaw

September 25, 2024

 

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ክልል በጂካዎ ወረዳ ትናንት ምሽት በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሰባት ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡

አደጋው የደረሰው ትናንት ምሽት 1 ሰዓት አካባቢ ከጋምቤላ ከተማ ወደ ኑዌር ዞን በመጓዝ ላይ የነበረ አምቡላንስ በጂካዎ ወረዳ የባሮ ወንዝ ጊዜያዊ ድልድይን ጥሶ ወንዝ ውስጥ በመግባቱ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በዚህም የሰባት ሰዎች ህይወት ወዲያው ሲያልፍ ሰባት ሰዎች ደግሞ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው የተገለፀ ሲሆን÷ ከሟቾቹ መካከል የጤና ባለሙያዎች እንደሚገኙበትም ታውቋል፡፡

በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ህክምና እየተከታተሉ መሆኑንና የአደጋው መንስዔም እየተጣራ መሆኑን ከክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡