አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ለ2017/18 የምርት ዘመን ከ66 ሚሊየን ኪዩቢክ ሜትር በላይ የተፈጥሮ አፈር ማዳበሪያ (ኮምፖስት) እንደሚዘጋጅ የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ገለጸ፡፡
የቢሮው ምክትል ሀላፊ አቶ ቃልኪዳን ሽፈራው የኮምፖስት ማዘጋጀት ስራ እየተከናወነ መሆኑን ጠቅሰው፤ እስካሁን ከ10 ማሊየን ኪዩቢክ ሜትር በላይ የተፈጥሮ አፈር ማዳበሪያ መዘጋጀቱን ጠቁመዋል።
የተፈጥሮ ማዳበሪያ የአፈር አሲዳማነትን በመከላከል በኩል የላቀ ሚና እንዳለው ገልጸው፤ በክልል ደረጃ 1 ነጥብ 8 ሚሊየን ሄክታር መሬት በተፈጥሮ ማዳበሪያ እንደሚሸፈን ተናግረዋል።
የደቡብ ወሎ ዞኑ ግብርና መምሪያ ሀላፊ አቶ አህመድ ጋሎ በበኩላቸው በዞኑ ከ8 ነጥብ 6 ሚሊየን ሜትር ኪዩቢክ በላይ የተፈጥሮ ማዳበሪያ ይዘጋጃል ብለዋል፡፡
በዚህም እስከ መሰከረም 30 የሚጠናቀቅ የተፈጥሮ ማዳበሪያ ዝግጅት ንቅናቄ በዞኑ ባሉ ወረዳዎች መጀመሩን ገልጸዋል።
በከድር መሀመድ