አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያን በዓለም ቱሪዝም ዘርፍ የሚያስተዋውቁ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን የቱሪዝም ሚኒስትር ዴዔታ ስለሺ ግርማ አስታወቁ፡፡
አቶ ስለሺ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደ ሀገር ያሉንን ሀብቶች በዓለም አቀፍ ደረጃ በማስተዋወቅ÷ ዘርፉ የሚያመነጨውን ሀብት ከፍ ለማድረግ በርካታ ሥራዎች እየተከናወኑ ነው ብለዋል፡፡
በዚህም ታዋቂ ግለሰቦችን፣ ሚዲያዎችን እና ሌሎች አካላትን በመጠቀም የማስተዋወቅ ሥራ መሆኑን አስረድተዋል፡፡