የሀገር ውስጥ ዜና

390 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

By Melaku Gedif

September 23, 2024

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 390 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

ተመላሾቹ ሁሉም ወንዶች ሲሆኑ÷ከእነዚህ መካከልም 7 ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡

ለተመላሽ ዜጎች ተገቢውን ድጋፍ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ሥራ እየተከናወነ መሆኑን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

ከሚያዚያ 4 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ በሚገኘው ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ሥራ እስካሁን ከ81 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ መቻሉ ተጠቁሟል፡