Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ሰሜን ኮሪያ የሴቶች ከ20 ዓመት በታች የዓለም ዋንጫን አነሳች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰሜን ኮሪያ ለሶስተኛ ጊዜ የሴቶች ከ20 ዓመት በታች የዓለም ዋንጫን አንስታለች፡፡

ይህም ከዚህ ቀደም ዋንጫውን ሶስት ጊዜ ማንሳት ከቻሉት ጀርመን እና አሜሪካ ጋር ታሪክ እንዲጋሩ አስችሏታል።

ሰሜን ኮሪያ በሴቶች ከ20 ዓመት በታች የዓለም ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ ጃፓንን 1 ለ 0 በማሸነፍ ነው ሻምፒዮን መሆን የቻለችው፡፡

የሰሜን ኮሪያን የማሸነፊያ ግብ የውድድሩ ኮከብ ግብ አግቢና ኮከብ ተጫዋች የሆነችው ቾይ ኢልሰን አስቆጥራለች፡፡

ይህ የሰሜን ኮሪያ የዓለም ዋንጫ ድል ሀገሪቱ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ከዓለም አቀፍ የስፖርት ውድድሮች ራሷን ካገለለች በኋላ የመጀመሪው ነው ተብሏል፡፡

ከፈረንጆቹ ነሀሴ 30 እስከ መስከረም 22 በኮሎምቢያ ቦጎታ ሲካሄድ የነበረው የሴቶች ከ20 ዓመት በታች የዓለም ዋንጫ ትላንት ምሽት ፍፃሜውን አግኝቷል፡፡

Exit mobile version