በርካቶች እንደ ወግና ልማዳቸው ዘመን የሚቀይሩበት፣ ይቅር የሚባባሉበት፣ አፈሩን ቀድሶ ምድሩን አለስልሶ ሀገር ያስረከባቸውን ፈጣሪ የሚያመሰግኑበት፣ ወጣቶች የሚተጫጩበት፣ የተበደለ የሚካስበት ነው መስከረም።
የኦሮሞ ሕዝብ ትውፊታዊ መገለጫ እሬቻ፣ የወላይታ የዘመን መለወጫ ዮዮ ጊፋታ፣ የሀዲያ የዘመን መለወጫ ያ ሆዴ ፣ የጋሞ የዘመን መለወጫ ዮ ማስቃላ፣ የካፊቾ የዘመን መለወጫ ማሽቃሮ፣ የጊዲቾ የዘመን መለወጫ ባላ ካዳቤ፣ የዘይሴ የዘመን መለወጫ ቡዶ ኬሶ፣ የቦሮ ሺናሻ የዘመን መለወጫ ጋሪ ዎሮ፣ የጎፋ የዘመን መለወጫ ጋዜ ማስቀላ፣ የኦይዳ የዘመን መለወጫ ዮኦ ማስቃላ፣ የከምባታ ዘመን መለወጫ መሳላ፣ የጠምባሮ ዘመን መለወጫ መሳላ፣ የዶንጋ ዘመን መለወጫ ዶንጊ ፉልታ፣ የየም ዘመን መለወጫ ሄቦ በጥቂቱ በመስከረም ወር ይከበራሉ።
እንደ ብልፅግና ፓርቲ በዓላቱ የሚመጥናቸውን ተገቢ የሆነውን ማህበራዊ እውቅና እንዲያገኙ፣ ህብረብሔራዊ አንድነታችንን ይበልጥ እንዲያጠናክሩ፣ በሀገራዊ የልማት መስክ ልዩ ትኩረት ለሰጠነው ለቱሪዝም ዘርፍ ተጨማሪ አቅም እንዲፈጥሩ እና ለአዎንታዊ ሰላም ግንባታ ውጥናችን አሻራ እንዲያሳርፉ ልዩ ትኩረት ሰጥተን መንቀሳቀሳችንን የምንቀጥል መሆኑን እየገለፅኩ በሁሉም አካባቢ ዘመን የምትለውጡ ኢትዮጵያውያን መልካም አዲስ አመት እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ።”
በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማዕከል ኃላፊ እና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ