የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያ በፓኪስታን የደረሰውን የሽብር ጥቃት አወገዘች

By ዮሐንስ ደርበው

September 23, 2024

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በፓኪስታን በከይበር ፓክቱንክዋ ግዛት በሀገሪቱ የኢትዮጵያ አምባሳደርን ጨምሮ ሌሎች ልዑኮችን ባካተተ የዲፕሎማቲክ ኮንቮይ ላይ የተፈጸመውን የሽብር ጥቃት ኢትዮጵያ አወገዘች።

ዲፕሎማቶቹን ሲያጅብ ለነበረው የሟች ፖሊስ ቤተሰብም መጽናናትን ተመኝታለች፡፡

የሽብር ጥቃቱን በጽኑ ያወገዘችው ኢትዮጵያ÷ ለፓኪስታን ሕዝብና መንግሥትም መጽናናትን መመኘቷን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡