Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የካሳንቺስ የልማት ተነሺዎች 239 የኮንዶሚኒየምና 110 የመንግስት መኖሪያ ቤት እጣ አወጡ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቂርቆስ ክ/ከተማ የካዛንቺስ አካባቢ የልማት ተነሺ ነዋሪዎች የመንግስትና የኮንዶሚኒየም መኖሪያ ቤት እጣ የማውጣት ስነ ስርዓቱ መካሄዱን ቀጥሏል።

በስድስት ቀናት ውስጥ የዛሬውን ጨምሮ 742 የካሳንቺስ የልማት ተነሺዎች የመንግስትና የኮንዶሚኒየም መኖሪያ ቤት እጣ በማውጣት ቤታቸውን እየተረከቡ እንደሆነ የአስተዳደሩ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመልክቷል።

ከወጣው ዕጣ መካከል 503 ባለ አንድ እና ባለ ሁለት መኝታ የመንግስት መኖሪያ ቤቶችን እንዲሁም 239 ስቱዲዮ የኮንዶሚኒየም ቤቶች መሆናቸው ተነግሯል።

በዚሁ መሰረት በአቃቂ፣ በቦሌ አራብሳ፣ ገላን፣ ፈረንሳይ ጉራራ እና ጃርሶ ሳይት የመኖሪያ መንደሮች ለባለእድለኞች ተደራሽ እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል።

የእጣ ማውጣት ስነ ስርዓቱ በቀጣይ ቀናትም እንደሚከናወን ተጠቁሟል።

የልማቱ ተነሺዎች ማንኛውም አይነት ቅሬታ ካለቸው ከባንቢስ ወደ ደንበል በሚወስደው የቤቶች ኮርፖሬሽን ወይም በክፍለ ከተማው አስተዳደር 10ኛ ፎቅ ወደተቋቋመው የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ በአካል በመቅረብ ወይም በ9065 ነፃ የስልክ መስመር ማቅረብ እንደሚችሉም ተነግሯል።

Exit mobile version