የሀገር ውስጥ ዜና

የ”ጋሪ ዎሮ” በዓል በአዲስ አበባ እየተከበረ ነው

By Melaku Gedif

September 22, 2024

አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የቦሮ ሺናሻ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ “ጋሪ ዎሮ” በዓል በአዲስ አበባ እየተከበረ ነው።

በአከባበር ሥነ-ሥርዓቱ ላይ በመዲናዋ የሚገኙ የብሔረሰቡ ተወላዶች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በሃገር ሽማግሌዎች ምርቃት የተጀመረው ክብረበዓሉ ችቦ በመለኮስ እና በተለያዩ ባህላዊ ክዋኔዎች እየተከበረ ይገኛል።

የቦሮ ሺናሻ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ “ጋሪ ዎሮ”በመስከረም ወር አጋማሽ የሚከበር በዓል መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

ጋሪ ዎሮ ስለ ህዝቦች አብሮነት ፣ሰላም እና አንድነት የሚነገርበት እንዲሁም ከፈጣሪ ምህረት የሚለመንበት በዓል መሆኑም በዚሁ ወቅት ተገልጿል።

የሺናሻ ብሔረሰብ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከሚገኙ ብሔር ብሔረሰቦች መካከል አንዱ ነው፡፡

በወንድሙ አዱኛ