የሀገር ውስጥ ዜና

የመስቀል ደመራና ኢሬቻ በዓላት ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲከበሩ ዝግጅት ተደርጓል – ቢሮው

By Melaku Gedif

September 22, 2024

አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የመስቀል ደመራና ኢሬቻ በዓላት ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲከበሩ አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉን የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ አስታውቋል።

የቢሮው ሃላፊ ሊዲያ ግርማ÷ባዓላቱ ባሕላዊ እና መንፈሳዊ እሴታቸውን ጠብቀው ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲከበሩ ተጨማሪ 11 ሺህ የሰላም ሰራዊት ማሰልጠን መቻሉን ተናግረዋል።

ከከተማው ሁሉም ክ/ከተሞች የተውጣጡ የሰላም ሰራዊት አባላት ጋር በፀጥታ ሥራ ዙሪያ ውይይት በማድረግ ስምሪት መሰጠቱን ጠቅሰዋል፡፡

የሰላም ሰራዊቱ እና የጸጥታ መዋቅሩ በጋራ በሰሩት ሥራ ከተማዋ ሰላሟ የተረጋገጠ መሆኑን ጠቁመው÷ከዚህ በላይ ለጸና ከተማዊ ሰላም ሁሉም በጋራ ሊሰራ እንደሚገባ አሳስበዋል።

በተለይም የመሰቀል ደመራና ኢሬቻ በዓላት በደማቅ ሁኔታ ተከብረው እንዲጠናቀቁ የከተማው ሕዝብ በሃላፊነት ሊሰራ እንደሚገባ ሃላፊዋ አስገንዝበዋል።

 

 

በይስማው አደራው