Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማንቼስተር ሲቲ ከአርሰናል የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በ5ኛው ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማንቼስተር ሲቲ ከአርሰናል ዛሬ የሚያደርጉት ጨዋታ በጉጉት ይጠበቃል ፡፡

በፕሪሚየር ሊጉ ቀን 10 ሰዓት ላይ ብራይተን ሆቭ አልቢዮን እና ኖቲንግሃም ፎረስት በአሜክስ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡

ምሽት 12፡30 ላይ ደግሞ ማቼስተር ሲቲ ከአርሰናል በኢቲሃድ ስታዲየም የሚያደርጉት ጨዋታ የሳምንቱ ተጠባቂ ፍልሚያ ነው፡፡

በቅርብ ዓመታት ከፍተኛ የሊጉ ተፎካካሪ የሆኑት ሁለቱ ክለቦች በተለይ በታክቲኩ ረገድ ሊኖራቸው የሚችለው ፉክክር በእግር ኳስ ቤተሰቡ ዘንድ በጉጉት ይጠበቃል፡፡

በአርሰናል በኩል ማርቲን ኦዴጋርድ እንዲሁም ሚካኤል ሜሪኖ በጉዳት ምክንያት የማይሰለፉ ሲሆን÷በማንቼስተር ሲቲ በኩል ደግሞ ናታን አኬ እና ኦስካር ቦብ በጨዋታው እንዳማይሳተፉ ተመላክቷል፡፡

Exit mobile version