ስፓርት

 ባሕር ዳር ከተማ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲን አሸነፈ

By Mikias Ayele

September 21, 2024

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2017 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ሣምንት ጨዋታ ባሕር ዳር ከተማ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲን 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡

ባሕር ዳር ከተማ ተጋጣሚውን ያሸነፈው ፍጹም ዓለሙ በመጀመሪያው አጋማሽ ባስቆጠራት ጎል ነው፡፡

ቀደም ብሎ በወልቂጤ ከነማ እና መቻል መካከል ሊደረግ የነበረው ጨዋታ የወልቂጤ ከተማ እግር ኳስ ክለብ አባላት ዝርዝር ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አለመላኩን ተከትሎ መቻል በፎርፌ አሸንፏል፡፡