ስፓርት

አትሌት ሰውመሆን የመጀመሪያ ዙር የተሳካ የዓይን ቀዶ ጥገና አድርጓል- ፌደሬሽኑ

By Mikias Ayele

September 21, 2024

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በልምምድ ላይ ሳለ በደረሰበት ጥቃት ግራ ዓይኑ ላይ ከፍተኛ ጉዳት አጋጥሞት የነበረው አትሌት ሰውመሆን አንተነህ የመጀመሪያ ዙር የተሳካ የዓይን ቀዶ ጥገና ሕክምና ማድረጉን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን አስታወቀ፡፡

ጉዳቱን ተከትሎ በሀገር ውስጥ ሕክምና ሲከታተል መቆየቱን እና ለተሻለ ሕክምና ወደ ሕንድ ቼይና ማቅናቱን ያስታወሰው ፌደሬሽኑ÷ አራት ሠዓታት የፈጀ የመጀመሪያ ዙር የተሳካ የዓይን ቀዶ ጥገና አድርጓል ብሏል፡፡

በአሁኑ ሠዓትም በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኝ እና ቀጣይ ሕክምናውን እየተከታተለ እንደሚገኝ መገለጹን የፌደሬሽኑ መረጃ አመላክቷል፡፡