Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የ”ጊፋታ” እሴቶች ለትውልድ እንዲሸጋገሩ እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበበ፣ መስከረም 11፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የወላይታ ዘመን መለወጫ “ጊፋታ” በዓል ባህላዊ እሴቶቹ ተጠብቀው ለትውልድ እንዲሸጋገሩ እየተሠራ መሆኑን የወላይታ ዞን ዋና አሥተዳዳሪ ጴጥሮስ ወልደማሪያም አስታወቁ፡፡

በዓሉ ሰላምን፣ አንድነትን፣ ፍቅርንና አብሮነትን የሚያጠናክር መሆኑን ጠቅሰው÷ የሥራ ባህልን ከማሳደግ አንጻር ጉልህ ድርሻ እንዳለው አስረድተዋል፡፡

በ”ጊፋታ” ባህላዊ የዕደ-ጥበባት ውጤቶች የሚታዩበትና የፈጠራ ሥራዎች የሚቀርቡበት መሆኑን የገለጹት ዋና አሥተዳዳሪው÷ ይህም የሀገር በቀል እውቀትን ለማጎልበት ያግዛል ብለዋል፡፡

“ጊፋታ” የሕብረተሰቡን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ በመሆኑ እሴቶቹና ትውፊቶቹ ተጠብቀው ለትውልድ እንዲሸጋገሩ በትኩረት እየተሠራ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የዞኑ ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ ምኅረቱ ሳሙኤል በበኩላቸው÷ “ጊፋታ” በሕዝቦች መካከል መረዳዳትና መቻቻልን የሚያጎለብት መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

Exit mobile version