Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የጎብኚዎች የቆይታ ጊዜን ለማራዘም እየተሠራ ነው – ሚኒስቴሩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በመስከረም ወር የሚከበሩ በዓላት ላይ ለመሳተፍ የሚመጡ የውጭ ሀገራት ጎብኚዎች የቆይታ ጊዜን ለማራዘም ዝግጅት መጠናቀቁን የቱሪዝም ሚኒስትር ዴዔታ ስለሺ ግርማ አስታወቁ፡፡

መስከረም ወር የተለያዩ ሐይማኖታዊና ሐይማኖታዊ ያልሆኑ በዓላት የሚከበሩበት ወቅት መሆኑን ገልጸው÷ በርከት ያሉ የውጭ ጎብኚዎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጡ አመላክተዋል፡፡

ሕብረተሰቡም በዓላቱን ትውፊቱን በጠበቀ መንገድ በማክበር የባህል ልውውጥ ከመፍጠር ባለፈ÷ ለጎብኚዎች ኢትዮጵያን ሊያስተዋውቅበት ይገባል ማታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

መንግሥት ሕዝባዊ በዓላት የሰላምና የአንድነት መገለጫዎች እንዲሆኑ ከማድረግ ባሻገር የውጭ ጎብኚዎች የተራዘመ ቆይታ እንዲኖራቸው የሚያስችሉ የበዓላት ጥቅል አገልግሎቶች ማዘጋጀቱንም ጠቅሰዋል፡፡፡

ለዚህም ሚኒስቴሩ ከክልሎችና ከሌሎች የዘርፉ ተዋንያን ጋር በመተባበር በኢትዮጵያ ያሉ የቱሪስት መዳረሻዎች እንዲተዋወቁ እያደረገ ነው ብለዋል፡፡

በ2017 በጀት ዓመት ከ1 ሚሊየን በላይ የውጭ ጎብኚዎችን ለመሳብ ታቅዶ እየተሠራ መሆኑን ገልጸው÷ ለመዝናናት፣ ለኮንፍረንስ፣ ለኤግዚቢሽንና ሌሎች ዓላማዎች የሚመጡ እንግዶችን ቆይታ ለማራዘም የተለያዩ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

Exit mobile version