Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

428 የካሳንቺስ አካባቢ የልማት ተነሺዎች መኖሪያ ቤት ተረከቡ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ቂርቆስ ክ/ከተማ የካዛንቺስ አካባቢ የልማት ተነሺዎች የመንግስት መኖሪያ ቤት እጣ የማውጣት ሥነ-ሥርዓት መቀጠሉን የከተማ አስተዳደሩ አስታውቋል፡፡

በዚህ መሰረትም በ3 ቀናት ውስጥ የዛሬውን ጨምሮ 428 የልማት ተነሺዎች የመንግስት መኖሪያ ቤት እጣ በማውጣት ቤታቸውን እንደተረከቡ ተገልጿል፡፡

ባለ 1 እና ባለ 2 መኝታ መኖሪያ ቤቶች በአቃቂ፣ አራብሳ፣ ገላን፣ ፈረንሳይ ጉራራ እና ጃርሶ ሳይት ለባለእድለኞች በወጣላቸው እጣ መሰረት እየተላለፉ ነው ተብሏል።

የእጣ ማውጣት ሥነ- ሥርዓቱ ነገን ጨምሮ በቀጣይ ቀናት እንደሚከናወን መገለጹንም የከተማዋ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

የልማቱ ተነሺዎች ማንኛውም አይነት ቅሬታ ካለቸው በክ/ከተማው አስተዳደር 10ኛ ፎቅ ወደተቋቋመው የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ በአካል በመቅረብ ወይም በ9065 ነፃ የስልክ መስመር በመደወል ቅሬታቸውን ማቅረብ እንደሚችሉ ተጠቁሟል።

Exit mobile version