Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ቀጣናዊ የምርምር ትብብርን ለ1 ዓመት እንድትመራ ተመረጠች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የአፍሪካ ቀጣናዊ የምርምር ትብብርን (ኤኤፍአርኤ) ለአንድ ዓመት እንድትመራ ተመርጣለች፡፡

ኤኤፍአርኤ የአፍሪካ ሀገራት የኒውክሌር ሳይንስና ቴክኖሎጂን ለሰላማዊ አላማ ለመጠቀም በፈረንጆቹ 1990 የመሠረቱት ሲሆን÷አሁን ላይ 44 አባል ሀገራትን በማካተት እየሰራ እንደሚገኝ ተጠቁሟል፡፡

ኢትዮጵያ 35ኛውን የኤኤፍአርኤ ቴክኒካል ቡድን ስብሰባን ሰኔ 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ማዘጋጀቷ ይታወሳል፡፡

ይህን ተከትሎም ኢትዮጵያ ከመስከረም 9 ቀን 2017 ጀምሮ የአፍሪካ ቀጣናዊ የምርምር ትብብርን ለአንድ ዓመት በሊቀመንበርነት እንድትመራ ተመርጣለች፡፡

ምርጫው የኢትዮጵያ ልዑካን እየተሳተፉበት በሚገኛው 68ኛው የኢንተርናሽናል አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ዓመታዊ ጉባኤ ጎን ለጎን ነው የተካሄደው፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ኢትዮጵያን በመወከል ኤኤፍአርኤን ለአንድ ዓመት በሊቀንበርነት ለመምራት ሃላፊነቱን ከአልጀሪያ ተቀብለዋል፡፡

ሃላፊነቱ ኢትዮጵያ የኒውክሌር ሳይንስና ቴክኖሎጂ የሚሰጠውን ዘርፈብዙ ጠቀሜታ በስፋት ለመተግበር ትችል ዘንድ ጉልህ ጠቀሜታ አንደሚኖረው ተጠቅሷል፡፡

Exit mobile version