ዓለምአቀፋዊ ዜና

የሂዝቦላ ከፍተኛ አዛዥ የሆነው ኢብራሂም አቂል ተገደለ

By Melaku Gedif

September 20, 2024

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በሊባኖስ ቤሩት ውስጥ እስራኤል በሰነዘረችው የአየር ጥቃት የሂዝቦላ ከፍተኛ አዛዥ የሆነው ኢብራሂም አቂል መገደሉ ተነገረ።

እስራኤል የሂዝቦላ ቡድን ከፍተኛ አዛዥ የሆነውን ኢብራሂም አቂልን ዒላማ አድርጋ የአየር ጥቃቱን መፈጸሟን የሊባኖስ የደህንነት ምንጮች እና የእስራኤል ጦር ራዲዮ ገልጸዋል።

በዚህም ከአዛዡ በተጨማሪ ስምንት ሰዎች የተገደሉ ሲሆን ሌሎች 59 ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን የሊባኖስ ጤና ሚኒስቴር መግለጹን ጠቅሶ ሬውተርስ ዘግቧል።