ስፓርት

በፕሪሚየር ሊጉ ሃድያ ሆሳዕና መቐለ 70 እንደርታን አሸነፈ

By Melaku Gedif

September 20, 2024

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2017 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር በዛሬው ዕለት በድሬዳዋ ስታዲየም ተጀምሯል፡፡

ቀን 10 ሰዓት ላይ በተካሄደው የመክፈቻ ጨዋታ ሃድያ ሆሳዕና መቐለ 70 እንደርታን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

የሃድያ ሆሳዕናን ብቸኛ የማሸፊያ ግብ ሄኖክ አርፍጮ በፍጹም ቅጣት ምት ከመረብ አሳርፏል፡፡

የሊጉ መርሐ ግብር ሲቀጥል ምሽት 1 ሰዓት ላይ አርባ ምንጭ ከተማ ከድሬዳዋ ከተማ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡