Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የ2017 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ዛሬ ይጀመራል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2017 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር በዛሬው ዕለት በድሬዳዋ ስታዲየም ይጀመራል።

በዚህ መሰረትም መቐለ 70 እንደርታ እና ሃዲያ ሆሳዕና ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ በድሬዳዋ ስታዲየም የሊጉን የመክፈቻ ጨዋታ ያካሂዳሉ፡፡

የሊጉ የመጀመሪያ ሳምንት መርሐ ግብ ሲቀጥል ምሽት 1 ሰዓት ላይ አርባ ምንጭ ከተማ ከድሬዳዋ ከተማ ይጫወታሉ።

በነገው ዕለት ደግሞ ወልቂጤ ከተማ ከመቻል ከቀኑ 10 ሰዓት እንዲሁም ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ከባህር ዳር ከተማ ምሽት 1 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ይሆናል፡፡

በ2017 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር 19 ክለቦች እንደሚሳተፉ የሊጉ መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version