ስፓርት

የ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የኮከቦች ሽልማት መርሐ ግብር ተከናወነ

By Melaku Gedif

September 20, 2024

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የኮከቦች ሽልማት እና የማጠቃለያ መርሐ ግብር በድሬደዋ ከተማ ተካሂዷል።

በዕለቱ በ7 ዘርፍ የዓመቱ ኮከቦች የተሸለሙ ሲሆን ፥ ለተሳታፊ ክለቦች እና ባለሜዳዎች የገንዘብ ክፍፍል ተደርጓል።

በዚህ መሰረትም የውድድር አዘጋጅ ባለሜዳዎች አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩንቨርሲቲ 4 ሚሊየን ብር፣ ድሬደዋ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ 3 ሚሊየን ብርና ሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ 3 ሚሊየን ብር ተሸልመዋል።

በሌላ በኩል በውድድርና ሥነ-ሥርዓት ኮሚቴ ከመስከረም 2012 እስከ ሐምሌ 2015 ላገለገሉት ለአቶ ሃብታሙ ሀይለሚካኤል፣ አቶ ሞገስ በሪሁን፣ አቶ ዮናስ ገብረማርያምና አቶ ኢቡሩሼ ዮሐንስ የእውቅና ሰርተፍኬት ተበረክቷል።

በተጨማሪም ለዓመቱ ኮከቦች በሰባት ዘርፎች የገንዘብና ልዩ ሽልማት ተበርክቷል።

* ኮከብ አሰልጣኝ – በፀሎት ልኡልሰገድ (200 ሺህ ብር)

* ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ – አሊ ሱሌማን (200 ሺህ ብር)

* ምስጉን ረዳት ዳኛ – ፋሲካ የኃላሸት (105 ሺህ ብር)

* ምስጉን ዋና ዳኛ – ባምላክ ተሰማ (105 ሺህ ብር)

* ኮከብ ግብ ጠባቂ – ፍሬው ጌታሁን (150 ሺህ ብር)

* ተስፈኛ ተጫዋች – ቢንያም አይተን (105 ሺህ ብር)

* ኮከብ ተጫዋች – ባሲሩ ኡመር (210 ሺህ ብር) መሸለማቸውን የሊጉ መረጃ ያመላክታል።