አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በብዝሃነት ላይ የተመሰረተ ሕብረብሔራዊ አንድነትን ለማጽናት የተጠናከረ የሕገ መንግስትና የፌደራሊዝም ሥርዓት ግንዛቤን መፍጠር ወሳኝ መሆኑ ተገልጿል፡፡
የኢፌዴሪ የሕገ መንግስትና ፌዴራሊዝም አስተምህሮ ማዕከል ከክልል ም/ቤቶች ጋር በትብብር መስራት በሚችልባቸው ጉዳዮች ላይ እየመከረ ነው፡፡
በመድረኩ የሁሉም ክልል ምክር ቤቶች እና ከተማ አስተዳደር ምክር ቤቶች እንዲሁም የብሔረሰብ ምክር ቤት ተወካዮች ተገኝተዋል፡፡
የማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር ሃይለኢየሱስ ታዬ (ዶ/ር)÷ ለፌዴራሊዝም እና ሕገ መንግስት አስተምህሮ ያለውን ዝቅ ያለ ግንዛቤ ማሻሻል ላይ ሁሉም ባለድርሻ ሊሆን ይገባል ብለዋል።
በተለይም በኢትየጵያ ውስጥ ያለውን በብዝሃነት ላይ የተመሰረተን ሕብረብሔራዊ አንድነት ለማጽናት የተጠናከረ የሕገመንግስት እና የፌዴራሊዝም ሥርዓት ግንዛቤን መፍጠር ወሳኝነት እንዳለው አስገንዝበዋል፡፡
በይስማው አደራው እና ብርሃን ደሳለኝ