ቢዝነስ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ጓንዡ የሚያደርገውን ሣምንታዊ በረራ ወደ 10 አሳደገ

By ዮሐንስ ደርበው

September 20, 2024

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከመስከረም 17 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ቻይና ጓንዡ የሚያደርገውን ሣምንታዊ የመንገደኛ በረራ ቁጥር ወደ 10 ማሳደጉን አስታወቀ፡፡

የበረራ ቁጥሩን ከማሳደጉ በፊት ወደ ከተማዋ የሚያደርገው ሣምንታዊ የበረራ መጠን ሰባት መሆኑን አየር መንገዱ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል፡፡