ስፓርት

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ በፓሪስ 2024 ኦሊምፒክ ለተሳተፉ አትሌቶች የዕዉቅናና ሽልማት መርሐ-ግብር አካሄደ

By Shambel Mihret

September 19, 2024

አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ በፓሪስ 2024 ኦሊምፒክ ለተሳተፉ አትሌቶች የዕውቅና እና የሽልማት መርሐ ግብር አካሄደ።

ታምራት ቶላ በማራቶን ብቸኛ ወርቅ በማስገኘቱ 2 ሚሊየን ብር ሲሸለም፥ በውድድሩ የብር ሜዳሊያ ያስገኙት ትዕግሥት አሰፋ፣ ፅጌ ድጉማና በሪሁ አረጋዊ እያንዳንዳቸው 1 ሚሊየን ብር ተበርክቶላቸዋል።

በውድድሩ አንድ ወርቅ እና አንድ ብር ያገኙ አትሌቶች አሰልጣኝ ገመዶ ደደፎ 1 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር ሲሸለም አሰልጣኝ ይረፋ ብርሃኑ የ800 ሺህ ብር ተሸላሚ ሆኗል።

ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ፣ ቀነኒሳ በቀለ፣ ኮማንደር ቶሌራ ዲንቃና ለሜቻ ግርማ አሰልጣኝ ሀጂ አዴሎ፣ ረዳት ኮሚሽነር ሁሴን ሼቦ ልዩ ተሸላሚ ሆነዋል።

በውድድሩ ላይ የተካፈሉ አትሌቶች፣ አሰልጣኞችና የቡድን አባላት ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

ከ33 ኦሊምፒክ ትምህርት ወስደን ለቀጣይ ተገቢውን ስራ መስራት ይገባል ሲሉም የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት አሸብር ወ/ጊዮርጊስ (ዶ/ር) ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ በ33ኛውኦሊምፒክ በ1 ወርቅና በ3 ብር በሜዳሊያ ሰንጠዡ 47ኛ ደረጃ ላይ ማጠናቀቋ ይታወሳል።

በወርቅነህ ጋሻሁን