የሀገር ውስጥ ዜና

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከዛምቢያ የእውቅና ሽልማት ተበረከተለት

By Melaku Gedif

September 19, 2024

አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከዛምቢያ ኤርፖርቶች ኮርፖሬሽን የእውቅና ሽልማት ተበርክቶለታል፡፡

ሽልማቱ የተበረከተው አየር መንገዱ ላበረከተው የላቀ አገልግሎት እና የላቀ የሥራ አጋርነት መሆኑ ተገልጿል፡፡

ሽልማቱ ለዛምቢያ ኤርፖርት ዕድገት በመንገደኛና በዕቃ ጭነት የአገልግሎት ዘርፎች የኢትዮጵያ አየር መንገድ ያበረከተው አስተዋጽኦና ያልተቋረጠ ድጋፍ ማሳያ ነው ተብሏል።

አየር መንገዱ የተበረከተለትን ሽልማት ኮርፖሬሽኑ 35ኛ ዓመቱን ባከበረበት ደማቅ መርሐ ግብር ላይ መረከቡ ተጠቁሟል፡፡