አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ለበርካታ ዓመታት በፖለቲካ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ የቆዩት የበየነ ጴጥሮስ (ፕ/ር) ስርዓተ ቀብር በጴጥሮስ ወጳውሎስ መካነ መቃብር ተፈፅሟል፡፡
በየነ ጴጥሮስ (ፕ/ር) ጳጉሜን 4 ቀን 2012 ዓ.ም የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ ሆነው በጠቅላይ ሚኒስትሩ ተሹመው ሲያገለግሉ መቆየታቸው የሚታወስ ነው፡፡
በኢትዮጵያ ለበርካታ ዓመታት በፖለቲካ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ ከቆዩ አንጋፋ ሰዎች መካከል አንዱ መሆናቸው የሚነገርላቸው በየነ ጴጥሮስ (ፕ/ር)÷ የተፎካካሪ ፓርቲው የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራሲ ፓርቲ ሊቀ-መንበር ሆነው ማገልገላቸው ይታወቃል፡፡
የተለያዩ ፓርቲዎችን በአባልነት የያዘውን የመድረክ ፓርቲንም በሊቀ-መንበርነት የመሩ ሲሆን ÷ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲም በመምህርነት እንዲሁም የትምህርት ምክትል ሚኒስትር ሆነው ማገልገላቸው የሚታወስ ነው፡፡
በታሪኩ ወልደሰንበት